የመንግስት ግዥ አገልግሎት ሠራተኞች ስለ አገራቸው ጉዳይ በግልጽና በባለቤትነት መንፈስ መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው! የኢትዮጵያ ምክክር ኮሚሽን ለፌደራል ተቋማት ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ፣ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት ሠራተኞች ስለ አገራቸው ጉዳይ በግልጽና በባለቤትነት መንፈስ መክረዋል፡፡* ይህ እድል በብዙ ዘመናት ውስጥ አንዴ የሚገኝ መልካምና ወሳኝ ዕድል በመሆኑ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል በማለት ሁሉም ሠራተኞች በሙሉ ልብና መነሳሳት ሃሳባቸውን፣ ጥያቄዎቻቸውንና ገንቢ አስተያየቶች በባለቤትነት መንፈስ ሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ አገራችን ያሉባትን ችግሮቿን በማያዳግም ሁኔታ *በምክክር ብቻ ትፈታለች*! የዚህ ታሪካዊ ክስተት ተካፋይ ትውልድ አካል በመሆናችንም ኮርተናል በማለትና በሚ/ር መ/ቤቱ ውይይት ላይ አገልግሎታችንን የሚወክል አንድ ተወካይ በመምረጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
በአገልግሎቱ የሪፎርም ስራ ላይ የሱፐርቪዥን ግምገማ እና ምልከታ ተካሄደ
በአገልግሎቱ የሪፎርም ስራ ላይ የሱፐርቪዥን ግምገማ እና ምልከታ ተካሄደ
A high-level meeting was held between H.E. Semereta Sewasew, State Minister of Finance of Ethiopia, and Dr. David Laborde
A high-level meeting was held between H.E. Semereta Sewasew, State Minister of Finance of Ethiopia, and Dr. David Laborde, Director of Agrifood Economics at the FAO, to reinforce cooperation on transforming Ethiopia’s agri-food systems.